በወላይታ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ማንቻ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
አደጋው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ከወላይታ ሶዶ ወደ ጎፋ በማምራት ላይ እንዳለ በፍሬን ብልሽት ምክንያት ከመንገድ ወጥቶ በመገልበጡ ነው የተከሰተው፡፡
በተከሰተው አደጋም ከሞቱት በተጨማሪ በ20 ሰዎች ላይ ከባድና በ45 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በወላይታ ሶዶ (ኦቶና) ሆስፒታል እና በሌሎች ጤና ተቋማት የሕክምና አገልግሎት እየተሰጣቸው መሆኑ ተጠቁሟል፡