በሕገ ወጥ በተያዘ 165 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ እርምጃ ተወሰደ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሸገር ከተማ አስተዳደር ሕገ ወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል በትኩረት እየሠራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ናስር ሁሴን ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ ሕገ ወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል በተሠራው ሥራ እስካሁን 165 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ማስመለስ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም 262 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ሕጋዊነቱ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡
ከተማው ፕላን እንዲኖረው ማድረግና የመሬት ሀብትን ማወቅ የመጀመሪያው ተግባር መሆኑን ጠቁመው÷ በዚህም የመሬት መረጃ አያያዝን ወደ ዲጂታል ማስገባት ተችሏል ነው ያሉት፡፡
ከ62 ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች ቋሚ የሥራ ዕድ መፈጠሩንም ነው አቶ ናስር በመግለጫቸው ያነሱት፡፡
በቀጣይ ከተማዋን ዘመናዊ በማድረግ ለዜጎች ምቹ እንድትሆን በፕላን ላይ የተመሰረቱ ተግባራት እንደሚከናወኑ አስገንዝበዋል፡፡
በለሊሴ ተስፋዬ