Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለትግራይ ክልል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለትግራይ ክልል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መልሶ ማቋቋሚያ ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ 11 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ሲሆን ፥ ቀሪው 1 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ኮምፒዩተሮች እና የህክምና መሳሪያ ቁሳቁሶች መሆናቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ልዩ አማካሪ ኢንጅነር ውብአየሁ ማሞ እንደተናገሩት ÷ ዛሬ በትግራይ ክልል ለሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መልሶ ማቋቋሚያ ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ዩኒቨርሲቲው መሰል ድጋፎችን በቀጣይነት ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀው ፥ በምርምርና ቴክኖሎጂዎች ረገድ በመልሶ ማቋቋሚያ ስራዎች ላይ የራሱን እገዛ እንደሚያደርግ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.