Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሕፃናት ቀንን በማስመልከት የችግኝ ተከላ መርሐግብር ተካሔደ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሰላም፣ፍቅር፣ እንክብካቤና ድጋፍ ለሁሉም ሕፃናት” በሚል መርህ የአፍሪካ የሕፃናት ቀን በአህጉር ደረጃ ለ33ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ32ኛ ጊዜ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

የችግን ተከላው በእንጦጦ ፓርክ የተካሄደ ሲሆን ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ የሕፃናት ፓርላማ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)÷ የነገው የሀገር ተረካቢ ትውልዶች እነዚህ ሕፃናት ናቸው ፤ በዚህም ዛሬ የተከሉት ችግኝ የነገ አሻራቸው በመሆኑ ሕፃናቱን ታሪካቸውን እንዲሰሩ ዕድል የፈጠረ ነው ብለዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ የከፋ ተፅዕኖውን እያደረሰ እንደሚገኝ የጠቀሱት ሚኒስትሯ በዚህም ቀዳሚ ተጎጂዎች ሴቶችና ሕፃናት በመሆናቸው ችግሩን ለመግታት ይህ እየተካሄደ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ ምሳሌ እንደሚሆን አንስተዋል።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሴቶችና ሕፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አለሚቱ ኡሞድ በበኩላቸው ÷ሕፃናትን በማሳተፍ ከአከባቢ ጥበቃው ጋር የተገናኙ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተከወኑ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ህፃናት ጤናቸው ተእንዲጠበቅና ስለኤች አይ ቪ ኤድስ በቂ ግንዛቤ ያላቸው ልጆች እንዲፈጠሩ ግንዛቤ ፈጠራ ላይ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት ተገልጿል።

በወንድሙ አዱኛ እና ላምሮት የኔዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.