Fana: At a Speed of Life!

ደብረ ማርቆስ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሟቾች ቁጥር 8 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ጎጃም ዞን ስናን ወረዳ ከረቡዕ ገበያ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የስምንት ሰዎች ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

የስናን ወረዳ ኮሙኒኬሽን መረጃ እንዳመላከተው በአደጋው አሽከርካሪውን ጨምሮ የስምንት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ÷ በ22 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ማረጋገጫ ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ቢምረው አሰፋ እንደገለጹት÷ የትራፊክ አደጋው የደረሰው በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር አብማ ክፍለ ከተማ እነራታ ቀበሌ 20 ልዩ ቦታው መሊት ጎጥ አካባቢ ባለው ቁልቁለት መንገድ ላይ ነው፡፡

አደጋው የደረሰው ከቀኑ 5፡ዐዐ ላይ መሆኑን ጠቁመው÷ ተሽከርካሪው ቁልቁለቱን በመውረድ ላይ ሳለ በአጋጠመው አደጋ መንገድ ስቶ መውጣቱን ተናግረዋል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው ነው ብለዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ማለታቸውን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.