Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስና አንበጣ ወረርሽኝ ተጽእኖ የ8 በመቶ የምርት ቅናሽ ሊያሳይ ይችላል- የግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የግበርናው ክፍለ ኢኮኖሚ አሁን በተከሰተው የኮሮና ቫየረስና የአንበጣ ወረርሽኝ በጋራ በሚፈጥሩት ተጽእኖ የ8 በመቶ የምርት ቅናሽ ሊያሳይ እንደሚችል የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አታ ሳኒ ረዲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ በተለይ ይህ የምርት ቅነሳ ሊያጋጥም የሚችለው በበልግ ወቅት፣ በበጋ መስኖ እና በመኸር ወቅት መሆኑን ገልጸዋል።

አሁን ያለንበት የበልግ ወቅትን ጨምሮ በሰብል ምርቶች እና በሆልቲካልቸር ወይም አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ላይ ኮሮና ቫይረስና አንበጣ ወረርሽኝ በሚያስከትለው ችግር ምክንያት ምርቱ እንደሚቀንስ ነው የገለጹት።

በዘንድሮው ዓመት 379 ሚሊየን ኩንታል ምርት የሚያስፈልጋት ኢትዮጵያ ማምረት የቻለችው ከሚያስፈልጋት 369 ሚሊየን ምትርቱን ነው።

የምግብ ዋስትናዋንም ለማረጋገጥ 20 ሚሊየን ስንዴና ሩዝ እንዲሁም መሰል ምርቶችን ከውጭ ማስገባት ነበረባት፤ በቫይረሱ ምክንያት ይህ ምርት የማይገባ ከሆነው ለቀጣይ ዓመት 40 ሚሊየን ኩንታል የምርት አጥረት ሊኖር እንደሚችል አቶ ሳኒ ገልጸዋል።

አሁን ላይ ያለው የምርት መጠን እና ክምችት እስከ ቀጣይ ዓመት ጥቅምት ወር በቂ መሆኑንም ሚኒስትር ደኤታው አክለው ተናግረዋል።

ሌላኛው በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ያለው የአንበጣ ወረርሽኝ 2 ከሞቶ የሚሆነውን የሃገሪቱን የቆዳ ስፋት የሚሸፍን ሲሆን፥ ይህ ማለትም 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ ተደራሽ መሆኑን አቶ ሳኒ አስታውቀዋል።

ይህን አደገኛ ፍጥነት ያለውንና በቶሎ የሚራባውን አንበጣ ለማጥፋትም በስድስት አውሮፕላኖችና ከኮሮና ራሳቸውን በጠበቀ መልኩ በሚሳተፉ የግብርና ባለሙያዎችን የአካባቢው ነዋሪዎች ለመከላከል እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የአንበጣ ወረርሽኙ በደቡብ ክልል እና ደቡብ ምእራብ ኦሮሞሚያ፣ ድሬዳዋ እንዲሁም አፋርንን ጨምሮ በሶስት ክልሎችና የከተማ መስተዳደርር አደጋ መድረሱን ገልጸዋል።

በዚህም 197 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል የሚገመት የማሽላ፣ የበቆሎ እና የስንዴ ምርትን እንዳወደመም ተናግረዋል።

አንበጣውንም ለማጥፋት የኬሚካል ርጭቱ በከፍተኛ ደረጃ እየተጠናከረ መሆኑን ገልጸዋል።

በኮሮናቫይረስና እና አንበጣ መንጋ ወረርሽኝ ምክንያት የሚቀንሰውን ምርት ለመተካትም የመስኖ አውታሮችን በስፋት በመጠቀምና ከዚህ በፊት ለጥጥና አገዳ እርሻ የሚያገለግሉ ቦታዎችን ሌሎች ሰብሎችን እንዲያመርቱ ከማድረግና አርሶ አደሩ ግብኣቶችን በቶሎ እንዲያገኝ ከማድረግ አንጻር 1 ቢሊዮን ዶላር ተመድቦ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ሳኒ ረዲ ገልጸዋል።

በፀጋዬ ንጉስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.