የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ በሶዶ ከተማ የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሒደትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በወላይታ ሶዶ ምርጫ ጣቢያዎች የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሒደትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
በወላይታ ዞን ሁለተኛው ዙር ሕዝበ ውሳኔ ምርጫ በተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ነው፡፡
በዞኑ 12 ጊዜያዊ የምርጫ ማስተባበሪያ ማዕከላት 1 ሺህ 812 የምርጫ ጣቢያዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
በወላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኙ 192 የምርጫ ጣቢያዎች ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ በሠላማዊ መንገድ ድምፁን እየሰጠ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በወላይታ ሶዶ ምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሒደቱን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
የዞኑ ተወላጅ የሆኑ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችም በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምጽ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡