በወላይታ ዞን ጊዜያዊ የሕዝበ ውሳኔ ድምፅ ውጤት ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ጊዜያዊ የሕዝበ ውሳኔ ድምፅ ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡
በዚሁ መሰረት በወላይታ ሶዶ ከተማ ጊዜያዊ የሕዝበ ውሳኔ አንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ ውጤት ይፋ መሆኑን ከዞኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ በወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማና ዳሞት ጋሌ ወረዳ ጊዜያዊ የሕዝበ ውሳኔ አንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ ውጤት ይፋ መሆኑ ተገልጿል፡፡
መራጩም በየመረጠበት ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ጊዜያዊ ውጤቱን እየተመለከተ ነው፡፡
ከቀናት በኋላ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተጠቃለለ ውጤት እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!