Fana: At a Speed of Life!

የወል እውነታዎች ላይ በማተኮር ሀገርን ማጽናት ይገባል – አፈ-ጉባዔ ታገሠ ጫፎ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የወል እውነታዎች ላይ በማተኮር ሀገርን ማጽናት እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሠ ጫፎ ገለፁ፡፡

“መፍጠንና መፍጠር፤ የወል ዕውነቶችን የማጽናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ” በሚል መሪ ሀሳብ ለምክር ቤት አባላት፣ ለሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽህፈት ቤቶች አመራሮችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቋል፡፡

በማጠቃለያው ላይ የተገኙት አፈ-ጉባዔ ታገሠ ጫፎ፥ በማያግባቡ ጉዳዮች ላይ በሰከነ መንፈስ በመነጋገር፣ በመተራረምና የወል የሆነ ዕውነታን በማፅናት ሀገርን ካጋጠማት ችግር ማሻገር ይገባል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ግጭቶች፣ አለመግባባቶች እና ጥርጣሬዎች መፈጠራቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ለችግሮች መነሻ የወል እውነታዎች ላይ ከማተኮርና የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከመግባባት ይልቅ የተናጠል እውነቶች ላይ በመንጠልጠል የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መግባባት ባለመቻል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ፣ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች እንደተገኙ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.