Fana: At a Speed of Life!

በ10 ዓመታት ውስጥ የከተሞች የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦትን ወደ 100 በመቶ ለማሳደግ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣይ 10 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ያለውን የከተሞች የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ወደ መቶ በመቶ ለማሳደግ መታቀዱን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

14ኛው ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ ከተሞች የውኃ አገልግሎት መድረክ በድሬዳዋ ከተማ ተካሂዷል፡፡

መድረኩ የተካሄደው የኢትዮጵያ ከተሞች የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ የአገልግሎት አሰራሮችን ማዘመን በሚል እሳቤ ነው፡፡

የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ አስፋው ዲንጋሞ በመድኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በቀጣይ 10 ዓመት በኢትዮጵያ ያለውን የከተሞች የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦትን ወደ መቶ በመቶ ለማሳደግ መታቀዱን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ገንዘብ የማይከፈልበትን የንጹህ መጠጥ ውኃ ከ39 በመቶ ወደ 20 በመቶ ለመቀነስ ይሰራል ብለዋል፡፡

የዘርፉን ችግሮች ለመቅረፍና የውኃ ተደራሽነት ለማስፋት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራርን በመከተል ለመስራት መታቀዱንም አስገንዝበዋል፡፡

በቲያ ኑሬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.