Fana: At a Speed of Life!

የኢጋድ ምግብ ደህንነት እና የድህረ ምርት ብክነት አስተዳደር ስትራቴጂዎች ላይ ያተኮረ ስብስባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) የምግብ ደህንነት እና የድህረ ምርት ብክነት አስተዳደር ስትራቴጂዎች ላይ ያተኮረ የሚኒስትሮች ስብስባ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ለሁለት ቀናት የሚቆየው ጉባኤ አላማ ስትራቴጂዎቹ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በጉባኤው ላይ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የኢጋድ አባል ሀገራት የግብርና ሚኒስትሮች፣ የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ተወካዮች እና ሌሎች የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ኢጋድ በፋኦ ድጋፍ አማካኝነት በሀገራት እና በቀጣናው የምግብ ደህንነት ስርዓትን ማጠናከር እና በምግብ ግብይት ውስጥ ፍትሐዊ አሰራሮች እንዲተገበሩ ማድረግን አላማ ያደረገ የምግብ ደህንነት ስትራቴጂ በፈረንጆቹ 2022 ማዘጋጀቱ ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል የኢጋድ የድህረ ምርት ብክነት አስተዳደር ስትራቴጂ በፈረንጆቹ 2018 መዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡

የምርት ብክነትን በመቀነስ በቀጣናው ብቁ እና የማይበገር ጠንካራ የምግብ ስርዓት መገንባት፣ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንዲሁም የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽነት እና የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል የስትራቴጂው አላማዎች መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.