Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ የታይዋንን መሪ እንዳትቀበል ቻይና ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ኬቨን ማካርቲ የታይዋንን መሪ ዛይ ኢንግ ዌን ተቀብለው እንዳያነጋግሩ ቻይና ጠየቀች፡፡

የታይዋንን መሪ ማነጋገር “የአንድ ቻይና”ን መርኅ እና ሉዓላዊነት መጣስ ነው ብላለች ቻይና፡፡

የቻይና እና የአሜሪካ መሪዎች በኢንዶኔዢያ ባሊ በጋራ ያወጧቸው ሦስት መግለጫዎች እንዲከበሩ ማሳሰቧንም ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ፥ ሁኔታው የቻይናን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በእጅጉ የሚጎዳ ነው ብለዋል፡፡

ቻይና ሁኔታውን በቅርበት እንደምትከታተል እና ሉዓላዊነቷን እንዲሁም የግዛት አንድነቷን በቆራጥነት እንደምታስከብር በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል አስታውቃለች፡፡

አሜሪካ በበኩሏ ሁኔታውን “አጋነሽዋል” ስትል ቻይናን ገሥጻ የታይዋን መሪ በአሜሪካ በኩል የሚያደርጉት “ትራንዚት” ቀደም ብሎ በመርሐ-ግብራቸው የተያዘና “መደበኛ” ጉብኝት ነው ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

የታይዋን ይፋዊ ያልሆነ ጉብኝት ከአሜሪካ ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ እንደሆነና የቻይናን ሉዓላዊነት እንደማይጋፋ የኋይት ሐውስ የብሔራዊ ደኅንነት ቃል-አቀባይ ጆን ኪርቢ ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.