Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ አጋርነቷን ለማጠናከር እየሠራች ነው – ወ/ሮ ሙፈሪሃት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያላትን አጋርነት ለማጠናከር እየሰራች መሆኗን የሥራ ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡

በሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የተመራ ልዑክ በጀርመን ሙኒክ ባካሄደው ጉብኝት÷ ትብብሮችን ለማጠናከር እና ተሞክሮዎችን ለመቅሰም ያለመ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ልዑኩ በቆይታው÷ ከኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የሥራ ፈጣሪዎች ፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና የማኅበራት ተወካዮች ጋር በሰው ኃይል ልማት እና ጀርመን በምትታወቅበት የሁለትዮሽ የትብብር ሥልጠና አስፈላጊነት ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በክኅሎት ልማት ዘርፍ ትልቅ ሚና ያለው የፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ዕውን ለማድረግ ከሙኒክ ቴክኒክኒካል ዩኒቨርሲቲ ጋር መሥራት በምትችልበት ሁኔታ ላይ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር መምከራቸውንም ገልጸዋል፡፡

የትብብር ማዕቀፉ በሁለትዮሽ የትብብር ሥልጠና ፣ በጥናትና ምርምር፣ በኢኖቬሽን፣ የግሉን ሴክተር ተሳትፎ በማሳደግ እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ መሆኑንም ነው ያመላከቱት፡፡

ትብብሩ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የሪፎርም ሥራ ውጤታማነት ላይ የራሱ አወንታዊ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.