ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በመካከላቸው በጊዜያዊ ፈቃድ ይሰጥ የነበረውን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ቋሚና ሁሉን አቀፍ በሆነ ስምምነት ለመተካት የሁለትዮሽ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ስምምነት ፈረሙ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪከ ገበያ ካለው የላቀ ድርሻ፣ ተመራጭነት እናአፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር ለማገናኝት ካለው ብቃት አንጻር በሀገራቱ መካከል የስምምነቱ መፈረም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ተብሏል፡፡
በሁለቱ ሀገራት መሀከል የተፈረመው ስምምነት ቀደም ሲል በጊዜያዊ ፈቃድ የሚደረጉ በረራዎችን ሕጋዊ ማዕቀፍ ይዘት እንዲኖራቸው ያስችላል መባሉን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም የአየር ትራንስፖርት አገልግሎቱን የዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ስታንዳርዶችና መርሆችን መሰረት ባደረገ መልኩ ለማከናወን መሰረት የሚጥል ስለመሆኑ ተጠቅሷል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ በቀን ሁለት ጊዜ መደበኛ በረራ ያደርጋል፡፡
በተጨማሪም የሁለቱ ሀገራት የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን መስሪያ ቤቶች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው መንግስቴ እና በደቡብ ሱዳን መንግስት በኩል ደግም አቻቸው ካፒቴን ሱቤክ ዴቪድ ዳዳ ናቸው፡፡
በተጨማሪም የሁለቱ ሀገራት የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን መስሪያ ቤቶች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የተስማሙ ሲሆን÷ በዛሬው ዕለትም በፈልጎ ማዳን (Search and Rescue) ላይ በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!