የሐረሪ ክልል ካቢኔ የቀረበለትን የበጀት ክለሳ አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ)የ2015 የበጀት ዓመት የ11 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም መነሻ በማድረግ የቀረበለት የበጀት ክለሳ አጽድቋል፡፡
ካቢኔው ያጸደቀው የ67 ሚሊየን 67 ሺህ 212 ብር የበጀት ክለሳ ነው።
የበጀት ክለሳው ያስፈለገው ተጨማሪ በጀት የጠየቁ ሥራዎች በመኖራቸው ነው መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የበጀት ክለሳው ለአዳዲስ ተቋማት አደረጃጀት፣ የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ብቃት ያለው የፖሊስ ኃይል አቅምን ለማጠናከር፣ ለሰብዓዊ ድጋፍ እና ለመደበኛ ሥራዎች ማስፈጸሚያዎችን በመለየት የበጀት እጥረት ላጋጠማቸው ጉዳዮች ይውላል ተብሏል።
በክልሉ በ2015 የበጀት ዓመት 11 ወራት ለሥራ ማስኬጃ የወጣው ወጪ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ70 ሚሊየን ብር በላይ መቀነስ መቻሉ ተጠቁሟል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!