Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቱርክ መንግስት ለኮቪድ -19 ወረርሽኝ መከላከል ተግባር የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በዛሬው እለት ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር አስረከበ።

ድጋፉ በዋነኝነት ለኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ተግባር የሚውሉ ሲሆን፥ 280 ካርቶን ወይም 1 ሺህ 700 ኪሎ ግራም የሆነ የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣ የኬሚካል ማጽጃዎች፣ የማጽጃ አልባሳት እና ሌሎችም ቁሳቁሶች ይገኝበታል።

የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት፥ የቱርክ መንግስት በዚህ አስከፊ ወቅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን በመሆን ላደረገው ድጋፍ አመስግነው፤ ይህም በሀገራቱ መካከል የጠበቀ ግንኙነት ለመኖሩ ትልቅ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል።

አያይዘውም ድጋፉ ወረርሽኙን ለመከላከል እንደ አገር እየተደረገ ላለው ርብርብም የበኩሉን እገዛ እንደሚያደረግ መግለፃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ሚስትረስ ያፕላክ አልፕ በበኩላቸው፥ በሁለቱ ሀገራት መካከል በባህል፣ በታሪክና በዲፕሎማሲው መስክ የቆየ ወዳጅነት መኖሩን አስታውሰው፤ በኢኮኖሚው ረገድም የሀገሪቱ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሱ መሆኑን ጠቁመዋል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.