ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ሀገር አቀፍ የጤና ዐውደ ርዕይ”ን አስጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ሀገር አቀፍ የጤና ዐውደ ርዕይ”ን ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም አስጀምረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷”ሀገር አቀፍ የጤና ዐውደ ርእይ” ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም አስጀምረናል ብለዋል።
በዐውደ ርዕዩ የመንግሥት እና የግል ተቋማት፣ በጤና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሠማሩ ድርጅቶች እንዲሁም የምርምር ተቋማት እንደሚሳተፉም ገልፀዋል፡፡