Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የኮሮናቫርሰ መከላከል ስራ 25 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ የኮሮናቫርሰ መከላከል ለምታደርገው ጥረት 25 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን ገለፀ።

ህብረቱ በቀጣይም ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የምታደርግውን ጥረት እንደሚደግፍ አስታውቋል።

የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት “#TeamEurope” የተባለ ኢኒሼቲቭ ማቋቋማቸውን የገለፀው ህብረቱ፥ ኢኒሼቲቩ የህብረቱ አባል ሀገራትና ከህብረቱ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ለኮሮናቫይረስን መከላከል የ20 ቢሊየን ዩሮ የድጋፍ ማእቀፍ ይፋ አድርጓል።

ኢትዮጵያም የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ለምታደርግው ጥረት በኢኒሼቲቩ አማካኝነት ድጋፍ እንደሚደረግ የአውሮፓ ሀብረት አስታውቋል።

በዚህም በአውሮፓውያኑ 2020 ለኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ የ200 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ እንደሚደረግም ተገልጿል።

ከዚህም ውስጥ 25 ሚሊየን ዩሮ በጤናው ዘርፍ በተለይም ኮቪድ 19 መከላከል ላይ ፈጣም ምላሽ ለመስጠት መለቀቁን ነው በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ቢሮ ያስታወቀው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.