Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ለመምራት ሴራሊዮን ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክን ለመምራት ሴራሊዮን ገቡ፡፡

የሴራሊዮን አጠቃላይ ምርጫ የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ይካሄዳል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ምርጫውን ለመታዘብ ለአጭር ጊዜ ያቋቋመውን ልዑክ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዲመሩት መምረጡ ይታወሳል።

በሴራሊዮን አጠቃላይ ምርጫ ድምጽ ለመሥጠት ከ3 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ዜጎች መመዝገባቸውን የሀገሪቷ የምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.