Fana: At a Speed of Life!

የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት አትሌቲክስ ሻምፒዮና የፍጻሜ ውድድሮች ተከናወኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተጀመረው 3ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት አትሌቲክስ ሻምፒዮና በተለያዩ ርቀቶች የፍጻሜ ውድድሮች ተከናውነዋል፡፡

በዚሁ መሰረት በ10 ሺህ ሜትር የወንዶች ውድድር÷ አቤል በቀለ ከተንታ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 1ኛ፣ ኃይሌ ጥጋቡ ከደብረ ብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 2ኛ እንዲሁም አንዳርጋቸው አዳሙ ከደብረ ብርሃን አትሌክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 3ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

በ100 ሜትር መሰናክል የሴቶች ውድድር÷ አበበች ተመስገን ከደብረ ብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 1ኛ፣ አሳመነች ማሙሽ ከቦሬ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 2ኛ እና ኤደን አንተናየሁ ከደብር ብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 3ኛ ሆነዋል፡፡

በርዝመት ዝላይ የወንዶች ውድድር ደግሞ÷ ባጥሶ ቱሞቻ ከሀገረ ሰላም አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 1ኛ፣ ንጋቱ ዋቶ ከቦሬ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 2ኛ እንዲሁም ወንድማገኝ ደገፋ ከተንታ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡

በርዝመት ዝላይ ሴቶች ውድድር÷ መሠረት መኮንን ከተንታ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 1ኛ፣ ትዕግስት ብርሃኑ ከተንታ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 2ኛ እና አዲሴ አለሙ ከተንታ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 3ኛ ደረጃ መያዛቸውን አትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.