Fana: At a Speed of Life!

ቅሬታንና አቤቱታን ባሉበት ማቅረብ የሚያስችል የኦንላይን አገልግሎት ስራ ላይ ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትህ ሚኒስቴር ውሳኔ ያገኙ የወንጀል መዛግብት ላይ ቅሬታና አቤቱታ ያላቸው ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው ማቅረብ የሚያስችላቸውን ኦንላይን አገልግሎት ስራ አስጀመረ፡፡

በሚኒስቴሩ የተቋም ግንባታና የሪፎርም ስራዎች ሚኒስትር ዴኤታ ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር)፥ የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የወንጀል መዛግብት ውሳኔዎች ላይ ተገልጋዮች የሚኖራቸውን ቅሬታና አቤቱታ ባሉበት ሆነው በአነስተኛ ወጪ፣ ጊዜ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ሳይንገላቱ እንዲያቀርቡ ታስቦ ድረ ገጹ መበልጸጉን ተናግረዋል።

አገልግሎቱ ለተገልጋይ ዜጎች፣ ለዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስራቸውን በብዙ መልኩ እንደሚያግዝ መግለጻቸውን የሚኒስሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በቀጣይም የወንጀል ፍትህ አስተዳደሩን በዚሁ መልኩ ለማደራጀት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ጉዳይ መከታተያ ዳይሬክተር ጌቱ ታደሰ በበኩላቸው÷ አገልግሎቱ በልደታ የሚገኙ የወንጀል ጉዳይ ዳይሬክቶሬቶች፣ በአዲስ አበባ በሚገኙ 10 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እንዲሁም በድሬዳዋና በሐዋሳ የሚገኙትን ጽ/ቤቶችን እንደሚያካትት አረጋግጠዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ማንኛውም ቅሬታና አቤቱታ ያላቸው ተገልጋዮች በ https://www.eservices.gov.et በመግባት ባሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.