አቶ ደስታ ሌዳሞ በሆኮ ወረዳ የተገነባውን ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት መረቁ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል ሆኮ ወረዳ የተገነባውን ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ፡፡
ትምህርት ቤቱ በግል ባለሃብት መገንባቱን የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
አቶ ደስታ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በክልሉ በትምህርት ዘርፍ ያለውን ስብራት ለመጠገን እንዲያስችል ጥራት ያለው ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል።
በክልሉ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋት ቃል በገባነው መሰረት በትምህርት፣ በውኃ፣ በመንገድ እና በሌሎች ልማቶች ሲዳማን እየገነባን ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።
የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በየነ በራሳቸው ÷ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ትውልዱን በእውቀት ጎዳና ለማነፅ እየሰሩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡