Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት በጦርነቱ ለተጎዱ አርሶ አደሮች ከ30 ሺህ ኩንታል በላይ ዘር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት እና ፈረንሳይ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች በጦርነቱ ለተጎዱ አርሶ አደሮች ከ30 ሺህ ኩንታል በላይ ዘር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት እና ፈረንሳይ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት እና የአማራና ትግራይ ክልሎች ግብርና ቢሮዎች ላከናወኑት ትልቅ ተግባር እውቅና ሰጥተዋል፡፡
የተደረገው ድጋፍ ለታለመላቸው ተጠቃሚዎች የሚደርስበትን ማስረጃ በመሰብሰብ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች በጦርነት ለተጎዱ አርሶ አደሮች የተሻሻለ ዘር እንደተከፋፈለ ተጠቅሷል፡፡
የጋራ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክቱ በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የግብርና ስራ እንደገና ለመጀመር እንደሚያስችል መገለጹንም የሕብረቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
አሁን ላይም 30 ሺህ ኩንታል በላይ ዘር ተገዝቶ ጉዳት ለደረሰባቸው 250 ሺህ ገበሬዎች እየተከፋፈለ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.