Fana: At a Speed of Life!

የምርጫ ቁሳቁሶቹንና ውጤቶቹን ከማዕከላት ወደ ዞኑ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የመሰብሰብ ሥራ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምርጫ ቁሳቁሶቹንና ውጤቶቹን ከ12ቱም ማዕከላት ወደ ዞኑ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የመሰብሰብ ሥራው መጠናቀቁን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የምርጫ ሂደቱ ቀጣይ ሥራ የሆነው የውጤት ማዳመሩ ከሰዓት ስለመጀመሩ የቦርዱ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በ1 ሺህ 812 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ያስፈጸመው የወላይታ ዞን የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ የምርጫ ቁሳቁስ÷ በ12ቱም ጊዜያዊ ማስተባበሪያ ማዕከላት የመሰብሰብ ሥራው ትናንት መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

ቦርዱ የሕዝበ ውሣኔውን ገለልተኛነት ለማረጋገጥ እንዲያስችል በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የተሻለ አፈጻጸም ካሳዩት አስፈጻሚዎች ውስጥ 5 ሺህ 215 አስፈጻሚዎች ከአዲስ አበባ መልምሎና አሠልጥኖ በዞኑ ባሉ 1 ሺህ 812 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ማሳተፉን አስታውቋል፡፡

በዛሬው ዕለትም ከወላይታ ሶዶ ወደ አዲስ አበባ ስለመመለሳቸው ነው የተመለከተው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.