Fana: At a Speed of Life!

ከ2 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥረናል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የሥራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ በተከናወኑ ሥራዎች ከ2 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡

ኢንተርፕራይዞችን ወደ ኢንቨስትመንት እንዲሸጋገሩ የክልሉ መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ድጋፍ ማድረጉን አቶ ሽመልስ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ይህም በአሁኑ ወቅት ኢንተርፕራይዞች ከ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል በማፍራት በኢኮኖሚው ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ ስለማድረጉ ጠቁመዋል፡፡

ሥራ አጥነትን በመቀነስ እና የተነቃቃ ኢኮኖሚ በመፍጠር ውስጥ የኢንተርፕራይዞች ሚና ወሳኝ መሆኑንም ነው አቶ ሽመልስ የገለጹት፡፡

በቀጣይም ኢንተርፕራይዞችን በመደገፍ፣ በማበረታታት እና በማሻገር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ በትኩረት ይሠራል ብለዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.