ቢዝነስ

በደብረ ብርሃን 38 ቢሊየን ብር ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

By Mikias Ayele

June 22, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ 38 ቢሊየን ብር ላስመዘገቡ 260 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ  መስጠቱን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ገለጸ።

እነዚህ ኢንቨስትመንቶች በሙሉ አቅማቸው ወደሥራ ሲገቡ ለ22 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ የመምሪያው  ኃላፊ  ብርሃን ገብረሕይወት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ቀድሞ ፈቃድ ካገኙ ኢንዱስትሪዎች መካከል 49 ያህሉ ግንባታቸው መጠናቀቁንም ገልጸዋል፡፡

ከእነዚህ መካከል 24 ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በደብረ ብርሃን ከተማ ከ720 በላይ ኢንቨስትመንቶች መኖራቸውን ጠቁመው÷ ከ545 በላይ የሚሆኑት ኢንዱስትሪዎች  ናቸው ብለዋል፡፡

በዘላለም ገበየሁ