በአዲስ አበባ ለ150 ሺህ 199 ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል- የትምህርት ቢሮ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ለ150 ሺህ 199 የስድስተኛ እና የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የትምህርት ቢሮው የፈተና እና ምዘና አስተዳደር ዳይሬክተር ዲናኦል ጫላ÷ ለፈተናው አስፈላጊው ሁሉ ዝገጅት ተደርጎ መጠናቀቁን ገልጸዋል።
በዚህም የ671 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ፣ የመፈተኛ ቦታዎች እና የፈተና ወረቀት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በአጠቃላይ ለ150 ሺህ 199 የስድስተኛ እና የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች በ185 የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናው እንደሚሰጥ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በመዲናዋ 75 ሺህ 107 የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ሰኔ 26 እና 27 ቀን የሚፈተኑ ሲሆን÷ ከሰኔ 28 እስከ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ደግሞ 75 ሺህ 92 የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ይፈተናሉ ብለዋል።