ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ አረንጓዴ ልማት ሽግግር ለማድረግ ለሚያስፈልገው የገንዘብ ድጋፍ ጠንካራ ዘዴ መፍጠር እንደሚገባ ተናገሩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፈረንሳይ ፓሪስ በአዲስ የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ስምምነት ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የ21ኛው ክፍለ ዘመን ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የባለብዙ ወገን ልማት ባንኮችን ሞዴል ማሻሻል” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ውይይት ላይ ነው የተሳተፉት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር÷ ወደ አረንጓዴ ልማት ሽግግር ለማድረግ ለሚያስፈልገው የገንዘብ ድጋፍ ጠንካራ ዘዴ መፍጠር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በተጨማሪም ከዚህ በፊት ቃል የተገቡ ስምምነቶችን በትክክል መተግበር እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት፡፡
የኮንሴሽናል ፋይናንስ አቅርቦትን ማሳደግ እና የዕዳ ቀውስን ማቆም እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡