በሰሜን ሸዋ መጤ ተምች በሰብል ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው ተባለ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአፍሪካ እና አሜሪካ መጤ ተምች ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ፡፡
በዞኑ አራት ወረዳዎች 27 ቀበሌዎች ላይ የተከሰተው የአፍሪካ ተምች ከ 5 ሺህ ሄክታር ሰብል በላይ ጉዳት ማድረሱን የመምሪያው የሰብል ልማት ቡድን መሪ አበበ ጌታቸው ጠቁመዋል፡፡
ተምቹ÷ በማሽላ፣ በቆሎና ጤፍ ላይ ጉዳት እንደሚያደርስም ነው አቶ አበበ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለጹት፡፡
እስካሁን ኬሚካልና ባህላዊ መንገድን በመጠቀም በ3 ሺህ 300 ሄክታር ላይ እየለማ ያለን ሰብል ማዳን ስለመቻሉም አስረድተዋል፡፡
እንዲሁም በስድስት ወረዳዎች ላይ የተከሰተው የአሜሪካ መጤ ተምች በ 5 ሺህ 300 ሄክታር በለማ ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱን አረጋግጠዋል፡፡
እስካሁንም በ2 ሺህ 800 ሄክታር ላይ የለማውን ሰብል መከላከል ተችሏል ነው ያሉት፡፡
በዞኑ የተከሰተውን የአፍሪካ ተምች ለመከላከል ኬሚካል እየቀረበ መሆኑን ገልጸው÷ የአሜሪካ ተምቹ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን እና መከላከያ ኬሚካል እየቀረበ አለመሆኑን አንስተዋል፡፡
አርሶ አደሩ በባህላዊ መንገድ እንዲከላከልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በምስራቅ አማራ በሚገኙ ዞኖች ተምች መከሰቱን አረጋግጦ÷ በክልሉ ለተከሰተው ተምች መከላከያ በቂ ኬሚካል በኮምቦልቻ ከተማ መቅረቡንና ግብርና መምሪያዎች መጠቀም ይችላሉ ብሏል፡፡
በአላዩ ገረመው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!