Fana: At a Speed of Life!

39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን ውድድር የፊታችን እሁድ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን ውድድር ሰኔ 18 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

መነሻ  እና መድረሻውን  ሰሚት  በሚያደርገው የማራቶን ውድድር ÷ 12 ክለቦች፣ 2 ክልሎችና 1 ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 354 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ይካፈሉበታል።

ለውድድሩ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ መዘጋጀቱን እና ከ1ኛ እስከ 8ኛ ለሚወጡ አትሌቶች ሽልማት እንደሚበረከት ተገልጿል፡፡

ለክልል፣ ለከተማ አስተዳደሮች፣ ለክለቦችና ለግል ተወዳዳሪ አትሌቶች  የሀገር ውስጥ የውድድር ዕድል በመፍጠርና ተተኪ የማራቶን አትሌቶችን ማፍራት የውድድሩ ዓላማ ነው ተብሏል፡፡

አትሌት ደጊቱ አዝመራው፣ ወርቅነሽ አለሙ ፣ኃይለማርያም ኪሮስ እና ሂርጶ ሸኖን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ አትሌቶች በውድድሩ እንደሚካፈሉ ተጠቁሟል፡፡

38ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን ውድድር ባለፈው ዓመት በባሕር ዳር ከተማ መካሄዱ ይታወሳል፡፡

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.