Fana: At a Speed of Life!

አምባቸው መኮንን(ዶ/ር) እና ጓዶቻቸው የተሰዉበት የመታሰቢያ መርሀ ግብር ተካሔደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳዳር አምባቸው መኮንን(ዶ/ር) እና ጓዶቻቸውየተሰዉበት 4ኛ ዓመት የመታሰቢያ መርሀ ግብር በአዲስ አበባ ተካሔደ፡፡

ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ. ም “በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ” አምባቸው መኮንንን(ዶ/ር) ጨምሮ እዘዘው ዋሴ እና ምግባሩ ከበደም መሰዋታቸው ይታውሳል።

በመታሰቢያ መርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ቤተስቦቻቸው ተገኝተዋል።

በመድረኩ የአምባቸው መኮንን(ዶ/ር) የህይወት ታሪክ ተተርኳል፡፡

ስለ አምባቸው መኮንን(ዶ/ር) እና ስለ ጎዶቻቸው የተለያዩ ግለሰቦች በመድረኩ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አምባቸው መኮንን(ዶ/ር) ስም የተሰየመ ፋውንዴሽን በአዲስ አበባ መመስረቱ ይታወሳል፡፡

በመድረኩም በአምባቸው መኮንን(ዶ/ር) ስም ፋውንዴሽን ይመስረት እንጂ አብረዋቸው የተሰዉ ጎዶቻቸውንም ለማስታወስ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ፋውንዴሽኑ በትምህርት ፣በጥናት እና ምርምር፣ በግብርና ፣ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተግባር ላይ በትኩረት እንደሚስራ በመድረኩ ተገልጿል።

ፋውንዴሽኑ እንዲጠናከርም ሁሉም የበኩሉን እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

በሲሳይ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.