የአየር ንብረት ለውጥ እና አረንጓዴ ዐሻራ ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን በአረንጓዴ ዐሻራ መዋጋት” በሚል መሪ ሐሳብ የአየር ንብረት ለውጥ እና አረንጓዴ ዐሻራ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
ውይይቱን ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢኒስቲትዩት ናቸው፡፡
ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ በመነሳት የአየር ንብረት ለውጥ እያሳደረ ያለው ተጽዕኖ ላይ የመፍትሔ ሐሳቦች በውይይ እንደሚነሱ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ተሞክሮ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ለቀጣናዊ ሰላም እና ደኅንነት እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ከባለድርሻ አካላት ባሻገር የማሕበረሰቡና የመገናኛ ብዙኃን ሚናን የተመለከቱ ጥናታዊ ጽሑፎች እንደሚቀርቡም ተጠቁሟል፡፡
የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም፣ የዜና አገልግሎት የቦርድ አባል እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፣ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር)፣ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ተቋማት እና ምሁራን፣ የዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በውይይቱ ተገኝተዋል።