የተባበሩት መንግሥታት ሥነ ሕዝብ ፈንድ በአፋር ክልል የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያሳድግ ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ከተባበሩት መንግሥታት ሥነ ሕዝብ ፈንድ (ዩ ኤን ኤፍ ፒ ኤ) የኢትዮጵያ ዋና ተጠሪ ካፊ ኩዋሜ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ዩ ኤን ኤፍ ፒ ኤ ለአፋር ክልል የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል በሚችልበት አግባብ ላይ መክረዋል፡፡
ተቋሙ የክልሉ የስነ ተዋልዶ እና የእናቶችን ጤና ለማሻሻል እንዲሁም ለአቅመ ደካማ ሴቶች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉ ተመላክቷል፡፡
ካፊ ኩዋሜ ÷የተባበሩት መንግሥታት ሥነ ሕዝብ ፈንድ ለአፋር ክልል የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያሳድግ ቃል ገብተዋል።
ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በበኩላቸው÷ ተቋሙ እስካሁን ለአፋር ክልል ላደረገው ዘርፈ ብዙ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡