Fana: At a Speed of Life!

አቶ አደም ፋራህ የምግባሩ ከበደ እውነቱ መታሰቢያ ሆስፒታልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) የምግባሩ ከበደ እውነቱ መታሰቢያ ሆስፒታልን ጎብኝተዋል፡፡

በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ በተገነባው የምግባሩ ከበደ እውነቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ጉብኝት መርሐ ግብር ላይ ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትም ተሳትፈዋል፡፡

በአካባቢው የሚገኙ አርሶ አደሮች የሆስፒታሉን አገልግሎት አሰጣጥ ለከፍተኛ ባለስልጣናቱ ማስረዳታቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ምግባሩ ከበደ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም “በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ” ሕይወታቸውን ካጡ ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.