Fana: At a Speed of Life!

የጤና ስርዓቱን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን ለማጠናከር በትብብር መስራት ይገባል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን ሀገር አቀፍ የጤና ዐውደ ርዕይ ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም “ባየናቸው ስራዎች በሀገራችን የጤና አገልግሎት እድገትን የሚያሳይ ተስፋ ሰጪ ለውጥ እንዳለ መረዳት ችለናል” ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

የጤና ስርዓቱን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን ለማጠናከርም ሁሉም በትብብር መስራት እንዳለበት አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ከተጀመሩ ስራዎች በተጨማሪ የግል ዘርፉን ተሳትፎ በማሳደግ ለዜጎች ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት በትብብር ሊሰራ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.