Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የህብረተሰቡ ድጋፍና ትብብር ሊጠናከር ይገባል – አቶኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የህብረተሰቡ ድጋፍና ትብብር ሊጠናከር እንደሚገባ ክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ አስገነዘቡ።

በጋምቤላ ክልል ሰላምና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ህዝባዊ ውይይት ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ተካሄዷል።

አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በወቅቱ እንደገለጹት÷ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ እየተደረገ ባለው ጥረት የህብረተሰቡ ሁለንተናዊ ተሳትፎ ሊጠናከር ይገባል።

በክልሉ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የተረጋጋ ሰላም ያለበትና አበረታች የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት በህዝቦች መካከል ግጭት በመፍጠር የክልሉን ሰላምና ልማት ለማደናቀፍ የሚሰሩ አካላት መኖራቸውን ጠቁመዋል።

በመሆኑም የክልሉ ህዝብ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችና አሉቧልታዎች በመመከት አንድነቱንና አብሮነቱን በማጎልበት ለክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት ጠንከሮ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የክልሉን ህዝቦች አብሮነትና አንድነት ለማሻከር የሚሰሩ ጽንፈኛ ኃይሎችን ለመንግስት አጋልጦ በመስጠት ረገድ ህብረተሰቡ ትብብሩን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።

በክልሉ የሚፈለገውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማ ማድረግ የሚቻለው ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ማስፈን ሲቻል እንደሆነ መጠቆሙንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ህዝቡ ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ለክልሉ ዘላቂ ሰላም ሰላም መረጋገጥ በትብብር ሊሰራ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡

ህዝቡ ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ለክልሉ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በትብብር ሊሰራ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.