Fana: At a Speed of Life!

የሲሚንቶና የድንጋይ ከሰል ምርትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል- ማዕድን ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲሚንቶና የድንጋይ ከሰል ምርትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የማዕድን ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ ከሲሚንቶና ከድንጋይ ከሰል አምራች ኩባንያዎች ጋር በ2016 በጀት ዓመት የምርት ዕቅድ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ ኩባንያዎቹ ምርታቸውን እንዲያሳድጉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት የሲሚንቶና የድንጋይ ከሰል ምርትን ለማሳደግ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ከውጭ የሚገባውን የድንጋይ ከሰል ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት ልዩ ትኩረት መሰጠቱንም ጠቁመዋል፡፡

የአገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል አምራቾች የድንጋይ ከሰል ምርት እና ጥራትን ሊያሳድጉ እንደሚገባም በውይይቱ ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

የኩባንያዎቹ የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው የመለዋወጫ እቃዎች፣ የጸጥታ እና የግብዓት ችግሮች እንዲቀረፉላቸው ጠይቀዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኩባንያዎቹን ችግሮች ለመፍታት አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለፁን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.