Fana: At a Speed of Life!

ለደቡብ ግንባር ሰራዊት ሆስፒታል የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ለደቡብ ግንባር ሰራዊት ሆስፒታል የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ።

በ18 ሄክታር ላይ የሚገነባው ሆስፒታል 4 ቢሊየን ብር የሚፈጅ ሲሆን፥ በሶስት ዓመት ተገንብቶ ለአገልግሎት ይበቃል ተብሏል።

የሆስፒታሉ አሰሪና ተቆጣጣሪ የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ መሆኑም ነው የተመለከተው።

በዝግጅቱ ላይ አምባሳደር ባጫ ደበሌ፣ የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ፣ ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋን እና ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.