Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፕሬዚዳንት ማክሮንን የአፍሪካ ሀገሮችን ለመደገፍ ላሳዩት ፈቃደኛነት አመሰገኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የአፍሪካ ሀገሮችን ለመደገፍ ላሳዩት ፈቃደኛነት ምስጋናቸውን አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሰሞኑን በፓሪስ በተካሄደው አዲስ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስምምነት ጉባዔ ላይ ተሳትፈዋል።
ከጉባኤው ጎን ለጎንም ከፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ “የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን በፓሪስ ላደረጉልን አቀባበል እና ሽኝት ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ፍሬያማ ለነበረው አዲስ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስምምነት ጉባዔ እንዲሁም የአፍሪካ ሀገሮችን ለመደገፍ ላሳዩት ፈቃደኛነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.