በ770 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የኮማንዶና የአየር ወለድ ዕዝ ካምፕ ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በ770 ሚሊየን ብር ወጪ በመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ የተገነባው የኮማንዶና የአየር ወለድ ዕዝ ካምፕ ተመርቋል፡፡
በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ፣በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌን ጨምሮ ከፍተኛ የሰራዊቱና የሲቭል አመራሮች ተገኝተዋል።
ለኮማንዶና የአየር ወለድ ዕዝ ለመኖሪያና ለስራ ታስቦ የተገነባው የወንዶ ጢቃ ፕሮጀክት 129 ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን÷ በውስጡ 214 ብሎኮች እንዳሉት ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዝግጅቱ ማጠናቀቂያ ላይ የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ከመሀንዲስ ዋና መምሪያ ካምፑን ይረከባሉ ፡፡