Fana: At a Speed of Life!

የጂቡቲ መንግስት የሀገሪቱን የፖሊስ የክብር ኒሻን ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ሸለመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጂቡቲ መንግስት የሀገሪቱን የፖሊስ የክብር ኒሻን ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ሸለመ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር፤ የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት ፕሬዚዳንት ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከጅቡቲ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልቃድር ካሚል መሀመድ የፖሊስ የክብር ኒሻኑን ተቀብለዋል።

46ኛ ዓመት የጅቡቲ ብሄራዊ ፖሊስ የምስረታ በዓል ቀን መከበሩንም የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራል ለሽልማቱ የበቁት የኢትዮ-ጂቡቲ ድንበር ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ በተለይም ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ በመከላከል ውጤት በመገኘቱ ነው ተብሏል፡፡

እንዲሁም በሁለቱ ሀገራት መካከል እየተፈጠረ ያለውን  ግንኙነትና ትብብር በማጠናከር በቀጣናው ከፍተኛ ለውጥ እንዲመጣ ላበረከቱት አስተዋፆ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ÷በጅቡቲ ብሄራዊ ፖሊስ የተሰጠው የፖሊስ የክብር ኒሻን ለእርሳቸው ብቻ ሳይሆን ለተቋሙ የተሰጠ ሽልማት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.