Fana: At a Speed of Life!

የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የሞጆ – ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ የግንባታ ሂደትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኘውን የሞጆ – ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ ጎበኙ።

የመንግስት የስራ ሃላፊዎቹ በአራት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተገነባ የሚገኘውን የ202 ነጠብ 6 ኪ.ሜ የፍጥነት መንገድ ግንባታ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።

በመስክ የስራ ቅኝቱም የትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሀብታሙ ተገኘ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የሞጆ – ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ ግንባታ ስራ ያለበት አጠቃላይ ደረጃ እና እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች ለሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ ተደርጎላቿል ፡፡

በዚህም መሰረት ኮንትራት አንድ እና ሁለት የፕጀክቱን 88 እና 81 በመቶ የግንባታ ስራ ያጠናቀቁ ሲሆን ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው ተብሏል።

የአዲስ አበባ -ሞያሌ-ናይሮቢ-ሞምባሳ የመንገድ ኮሪደር አካል የሆነው የሞጆ-ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክትከ 13 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ነው እየተገነባ የሚገኘው፡፡

32 ሜትር የመንገድ ስፋት ያለው ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በግራና በቀኝ በአንድ ግዜ 4 ተሸከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል ይሆናል

በፕሮጀክቶቹ ላይ ያሉ ተግዳሮቶችን በመፍታት የግንባታ ስራው እንዲፍጠን መንግስት ርብርቡን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሚኒስትር ድኤታው አቶ ካሳሁን ጎፌ ተናግረዋል።

ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ በበኩላቸው የኮሮና ቫይረስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ አሉታዊ አስተዋጾውን እንዳያሳርፍ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ስራዎች እየተከወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የመንገዱ መገንባት ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅን በማስቀረት በመስመሩ ላይ የሚገኙትን ወረዳዎች ፣ ከተሞችና የእርሻና የኢንዱስትሪ ቦታዎችን እንዲሁም የቱሪስት መስህብ የሆኑ ቦታዎችን ለማገናኘት ፋይዳው ከፍ ያለ በመሆኑ እንዲጠናቀቅ የክትትልና የቁጥጥር ሂደቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣናት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.