Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ አካባቢዎች ለጥፋት ዓላማ ሊውል የነበረ የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃዊ ወረዳ እና በማዕከላዊጎንደር ዞን ሳንጃ ኬላ ለጥፋት ዓላማ ሊውል የነበረ የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ፡፡

በጃዊ ወረዳ ፈንድቃ ከተማ በሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ለጥፋት ዓላማ ሊውል የነበረ 98 ፋልኮን ቱርክ ሰራሽ ሸጉጥ፣ 2 ክላሽን ኮቭ  ጠመንጃ፣ 171 የክላሽ ተተኳሽ ጥይት፣ 3 የክላሽ መጋዘን እና ሌሎች መሣሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ ማዕከላዊጎንደር ዞን ሳንጃ ኬላ 98 ሽጉጦች እና ሌሎችም ቁሶች በሕብረተሠቡ ጥቆማ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.