Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ከ33 ሺህ በላይ የፊት ጭንብሎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምንጩ ያልታወቀ እና ደረጃቸውን ያልጠበቁ ከ33 ሺህ በላይ የፊት መሸፈኛ ማስኮች እና 4 ሺህ 452 ሊትር የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ተያዘ።

የአዲስ አበባ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የኮሮና ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ጤና ተቋማት እና የመድሀኒት መደብሮች ላይ ምልከታ አድርጓል፡፡

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ደብረወርቅ ጌታቸዉ እንደገለጹት የኮቪድ 19 ወረርሽን መከሰትን ተከትሎ በከተማዋ ባሉ የጤና ተቋማት በተለይ በመድሀኒት መደብሮች ላይ በተደረገ የቁጥጥር ስራ ምንጩ ያልታወቀ እና ደረጃቸውን ያልጠበቁ ማስኮችን እና የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ተይዟል።

ምርቶቹንም የማስወገድ እና የማሸግ እርምጃ መወሰዱን  መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም በመጋዘናቸዉ እያለ የለም ብለዉ ደብቀዉ የተገኙ እና የማይገባ የዋጋ ጭማሪ ባስከፈሉ በጠቅላላው 147 የመድሀኒት መደብሮች ላይ አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው አቶ ደብረወርቅ ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ለማምረትም ከ22 በላይ የአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ከተስማሚነትና ምዘና ኤጀንሲ የብቃት ማረጋገጫ በመውሰድ ወደ ምርት ስራ እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን አቶ ደብረወርቅ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.