Fana: At a Speed of Life!

በአብርሆት ቤተመጻሕፍት የዲጂታላይዝ አገልግሎት ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአብርሆት ቤተ መጻህፍት የዲጂታላይዝ አገልግሎት ስራን አስጀመሩ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ “ዛሬ በአብርሆት ቤተመጻሕፍት የዲጂታላይዝ አገልግሎት ስራን አስጀምረናል” ብለዋል፡፡

ቤተ መጻህፍቱ አሁን በሚሰጠው አገልግሎት በአማካይ በቀን ከ15 ሺህ በላይ አንባቢዎችን የሚያስተናግድ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ዛሬ በተጀመረው እና 80 ሺህ መፅሃፍት ዲጂታል የተደረገበት አገልግሎት ከእጥፍ በላይ አንባቢዎችን መድረስ እንደሚያስችል ነው የተናገሩት፡፡

“ትውልዱ የሚያነብበት ስፍራ በማጣቱ እንጂ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት በንባብ ራሱን ለማነጽ የሚተጋ መሆኑን አይተናል” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

“ስለሆነም ተጨማሪ አዳዲስ ቤተመጻህፍት በየክፍለ ከተሞቻችን እየገነባን የተጠናቀቁትንም በቁሳቁስ እንዲሟሉ በማድረግ አንባቢ እና ምክንያታዊ ትውልድ ማፍራታችንን እንቀጥላለን” ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.