Fana: At a Speed of Life!

የውሃ ሀብት አስተዳደርና ኢነርጂ የባለድርሻ አካላት ፎረም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 11ኛው የዋሽ፣ የውሃ ሀብት አስተዳደርና ኢነርጂ ዘርፈብዙ የባለድርሻ አካላት ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በውይይት መድረኩ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር)፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ÷ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፣ የኢነርጂ ልማት፣ ንፁህ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አቅርቦትን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
መጠጥ ውሃን በተመለከተ በ2030 ሁሉም በሚባል ደረጃ በየአቅራቢያው ንፁህ ውሃ ማግኘት በሚችልበት ደረጃ እየተሰራ መሆኑን መግለፃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው÷ በጤናው ዘርፍ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የበለጠ ለማረጋገጥ 551 የሳኒቴሽን የግብይት ማእከላት ተቋቁመው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
መድረኩ ንፁህ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን እንዲሁም የኢነርጂ አቅርቦትን የተሻለ ለማድረግ በጋራ የምንሰራበትን ምቹ ሁኔታ የሚፈጥርና ወደ ተሻለ ለውጥ የሚያሻግር መሆኑን ገልፀዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.