ስፓርት

ዋሊያዎቹ ወደ አሜሪካ ተጉዘው የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

By Mikias Ayele

June 26, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ በመጓዝ የወዳጅነት እና የልምድ ልውውጥ ጨዋታዎችን ሊያደርግ ነው፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው÷የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከካረቢያኑ ጉያና ብሄራዊ ቡድን ጋር ሐምሌ 26 በዋሺንግተን ዲሲ ሴግራ ፊልድ ስታዲየም እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም ሐምሌ 29 ከትላንታ ሮቨርስ ክለብ ጋር በአትላንታ ሳውዘርን ክሬሰንት ስታዲየም ጨዋታውን እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡

ቀደም ሲል ብሄራዊ ቡድኑ ጨዋታዎችን በመጪው ሐምሌ 1 ለማድረግ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም ጨዋታዎቹ በሐምሌ 26 እና 29  ቀን 2015 ዓ.ም እንዲደረጉ መወሰኑን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡