በጋምቤላ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከፊታችን ሰኔ 26 ቀን ጀምሮ ይሰጣል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 26 እስከ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ ሙሴ ጋጄት ÷ክልል አቀፍ ፈተናውን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልፀው ÷በ205 የፈተና ጣቢያዎች 670 ፈታኞች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡
በፈተናው ላይ 12 ሺህ 805 ወንድ እና 9 ሺህ 746 ሴት ተማሪዎች በድምሩ 22 ሺህ 551 የቀንና የማታ ተማሪዎች እንደሚቀመጡ መግለጻቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ፈተናው በሚሰጥበት ቀንም ሆነ የፈተናው የጥያቄ ወረቀት የማጓጓዝ ሂደቱ ሰላማዊ እንዲሆን በየዘርፉ የሚገኙ የፀጥታ አካላት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡