የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የአረፋ በዓል በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በመላው ኢትዮጵያ በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት አድርጎ ፀጥታ የማስከበር ሥራውን እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡
የጋራ ግብረ ኃይሉ 1 ሺህ 444ኛውን የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም አስተላልፏል፡፡
በዓሉ በመላው ኢትዮጵያ በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት አድርጎ ፀጥታ የማስከበር ሥራውን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡
የእስልምና እምነት ተከታዮች በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከፀጥታና ደህንነት አካላት ጎን በመቆም የዜግነት ድርሻቸውን እንዲወጡም አሳስቧል፡፡
አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች እንዲሁም በስልክ ቁጥር +251 111 11 01 11፣ +251 115 52 63 03፣ +251 115 52 40 77፣ +251 115 54 36 78 እና +251 115 54 36 81፣ +251 115 54 36 84፣ +251 115 54 38 04 ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል አሳውቋል፡፡
በተጨማሪም +251 115 31 22 08፣ +251 115 31 22 23፣ +251 115 31 22 47፣ +251 115 31 22 20፣ +251 115 31 20 63፣ +251 115 31 20 33፣ +251 115 31 21 31፣ +251 115 31 22 21፣ +251 115 31 20 42፣ +251 115 31 20 05 ጥቆማዎችን በፍጥነት በመስጠት ወይም በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች መረጃውን በአካል በማድረስ ህብረተሰቡ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የጋራ ግብረ ኃይሉ ጥሪ ማቅረቡን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡