Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ-ቴሌኮም እና ንግድ ባንክ በጋራ የዲጂታል ፋይናስ አገልግሎት መሥጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮ -ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፋይናስ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የዲጂታል የፋይናስ አገልግሎትን በጋራ አስጀመሩ።

በሁለቱ ተቋማት ይፋ የሆነው አገልግሎት ÷ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለደንበኞቹ የሚሰጠውን አገልግሎት ተጠቃሚዎች ወደ ባንኩ መሄድ ሳይጠበቅባቸው ቴሌብርን በመጠቀም ባሉበት ቦታ የቁጠባ፣ የብድርና ሌሎች የፋይናስ አገልግሎቶችን ማግኘት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ለዚህም “አድራሽ”፣ “ስንቅ”፣ “ድልድይ” እና “እንደራስ” የተሰኙ አገልግሎቶች ይፋ ተደርገዋል።

በቤተልሔም መኳንንት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.